አድዋ መታወቂያችን፤ ምኒልክ ታዳጊያችን (ኃይሌ ላሬቦ፣ ዶ/ር)

በዚህ ወር መግቢያ ላይ ኢትዮጵያዉያን የአድዋን መቶ ኻያኛውን ያመት በዓል በያሉበት በአድናቆት አክብረውታል። በየሬድዮ ጣቢያዎቹ፣ በየፓልቶኮቹ፣ በየማኅበራዊ ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን በየተሰበሰቡበት ሁሉ ስለአድዋ ያልተናገረ፣ ያላሰበ፣ ወኔው ያልተቀሰቀሰ የለም ማለት ይቻላል። እንደታላቅነቱና ታሪክነቱ ከሆነ፣የአድዋ ድል ያንድ ቀን ብቻ በዓል መሆን የለበትም። የትም
አገር ሂደን ታሪክ ብንመረምር፣ መዛግብታቸውን ብንገለባብጥ፣

የአድዋን ዐይነት ታሪክ የሠራ ሕዝብም አገርም የለምና። የአድዋ ድል አሜሪቃ ነፃነቷን ካገኘችበት ድል፣ ከፈረንሳይና ከሩሲያ አብዮት፣ የደቡብ አፍሪቃ ጥቊሮች በጨቋኞቻቸው ነጮች ላይ ካገኙት የእሪና ድል እጅግ ይበልጣል። ጦርነቱ ከውጩ ሲታይ በሁለት ራሳቸውን በቻሉ ነፃና ልዑላን በሆኑ አገሮች መካክል ቢሆንም፣ ጥያቄው ቀጥለን እንደምናየው ስለሰው ዘር መብትና እኩልነት ነው። >>>>>>>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *