ትግሬዎች “እኔም ወልቃይቴ ነኝ!” እያሉ የወያኔ ወረራ በማውገዝ ለታሪክ ያስመዝግቡ!(ጌታቸው ረዳ – ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

በርዕሱ የተመለከተ ማሳሰቢያ ግልጽ ላድርግ። በቁጥር 8 የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ባለፈው ወር “እኔ ኦሮሞ ነኝ” የሚል በፌርማቸው ያረጋገጡት ለኦሮሞዎች እንቅስቃሴ ድጋፍ መለጋሰቸው ይታወሳል። ድጋፍ መለገሳቸው እንዳልተቃወምኩ፤ ነገር ግን አማራ ሲጠቃ ተመሳሳይ ‘ፌርማን ያሰባሰበ’ ድጋፍ ባለመስጠታቸው ‘ቅሬታ መግለጼ’ ባለፉት ጽሑፎቼ ያነበባችሁት ነው። ሰሞኑን በወልቃይት አማራ ላይ የትግሬ የበላይነት የተረጋገጠበት አሰራር ትክክል እንዳልሆነ በልዑል ራስ መንገሻ አማካኝነት የተሰጠው ምስክርነት ይፋ በመሆኑ፤‘እኔም ኦሮሞ ነኝ” ብለው የነገሩን ትግሬዎች ፤ ዛሬ ‘በስማቸው’ በአማራ ወልቃይት እና በመሳሰሉት አማራዎች’ እየተፈጸመ ስላለው የትግራይ ፋሺስቶች የበላይነት እርምጃ ማውገዝ ስለሚገባቸው “እኔም ወልቃይቴ ነኝ ብለው ድጋፋቸው ይስጡ” የምለው ምክንያት ለዚህ ነው። ማሳሰቢያው ለነዚህ ወንድሞችና እህት ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ለማላው የትግሬ ተወላጅ የሚመለከት ጥሪ ነው።

እህት ብቻ የሚመለከት ሳይሆን ለማላው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *